ወደ ሐመር ድህረገጽ እንኳን ደህና መጣችሁ።
ሐመር የሚባለው ሕዝብ በደቡብ ኦሞ ዞን ከጂንካ በታች በ100ኪ.ሜ ላይ ይገኛሉ። ወረዳው ሐመር ወረዳ ተብሎ ይጠራል ሐመር በጣም የሚታወቁት እንግዳን በመቀበል እንዲሁም ታላላቆቻቸውን በማክበር ይታወቃሉ።ኑሯቸው ከብት በማረባትና እርሻ በማረስ ላይ የተመሰረተ ነው። ሐመር ከሌላው ብሄር የሚለዩበት ሚስት ለማግባት ከብት ላይ መዝለል ይኖርበታል። ይህን ካላደረገ ጋብቻ ቢፈጽምም እንደባህሉ መሰረት ተቀባይነት አይኖረውም።
እነዚህ የምታዩዋቸው ሁለቱ ልጃገረዶች የሐመር ልጆች ናቸው። አለባበሳቸ ባህላዊ የሐመር አለባበስ ሲሆን በሐመር አካባቢ አሁን አሁን እየቀረ እየመጣ ነው። አናታቸው ላይ ያደረጉት ስሙ በላ ሲባል የውበት ምልክት ነው።